Genesis 33
1 ያዕቆብ ቀና ብሎ አየ። ዔሳው ወደ እርሱ እየመጣ ነበር። አራት መቶ ሰዎች ከኋላው ይከተሉት ነበር! ያዕቆብ ልጆቹን ለልያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮች አከፋፈላቸው።
3 ያዕቆብ ከፊት ወጣ። ወደ ወንድሙም ሄደ። ዔሳው ዘንድ እስኪደርስ ሰባት ጊዜ መሬት ላይ ወድቆ ፊቱን ደፋ።
4 ዔሳው ሮጠ! እጆቹን በያዕቆብ ላይ ጥሎ አጥብቆ አቀፈው። አንገቱን ደጋግሞ ሳመው። ሁለቱም አለቀሱ።
17 ያዕቆብ ወደ ሱኮት ሄደ። ቤት ሠራ፣ ለእንስሳቱም ትናንሽ ዳሶችን ሠራ። የቦታው ስም ሱኮት የተባለው ለዚህ ነው። ትርጉሙም ትናንሽ ዳሶች ማለት ነው።
18 በመጨረሻም ያዕቆብ በከነዓን ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ ደረሰ። የመጣውም ከጳዳን አራም ነበር። ከከተማይቱ ውጭ ድንኳኑን ተከለ።