Genesis 1
1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ሠራ፣ ከታች ያለውን መሬት፣ ከላይ ያለውን ሰማይ።
6 እግዚአብሔር እንደገና ተናገረ። «ውሃውን ለሁለት የሚከፍል ጠፈር ይሁን» አለ።
9 እግዚአብሔር እንደገና ተናገረ። «ውሃው ወደ አንድ ቦታ ይሰብሰብ። የደረቀ መሬት ይታይ» አለ። እንዳለውም ሆነ።
11 እግዚአብሔር እንደገና ተናገረ። «ምድር ዕፅዋትን ታብቅል። ሣር። በውስጣቸው ዘር ያላቸውን የፍራፍሬ ዛፎች» አለ። እንዳለውም ሆነ።
14 እግዚአብሔር እንደገና ተናገረ። «ቀኑን ከሌሊት የሚለዩ ብርሃናት በሰማይ ላይ ይንጠልጠሉ። ወቅቶችን፣ ቀናትን እና ዓመታትን ያመልክቱ» አለ።