Genesis 2
7 ያህዌ እግዚአብሔር ከመሬት አፈር ዘገነ። ሰውን አበጀው። ዝቅ ብሎም በሰውየው አፍንጫ ውስጥ እፍ አለበት። የሰውየው ደረት ተነሣ። ሕያው ሆነ!
8 ያህዌ እግዚአብሔር ራቅ ብሎ በምሥራቅ በኩል፣ በኤደን የአትክልት ስፍራ ተከለ። ሰውንም እዚያ አኖረው።
9 ያህዌ እግዚአብሔር ዛፎችን ከመሬት አበቀለ። የሚያማምሩ ዛፎችን። በጥሩ ፍራፍሬ የከበዱ ዛፎችን። በአትክልት ስፍራው መካከል ደግሞ ሁለት ዛፎች ነበሩ፣ የሕይወት ዛፍ እና መልካምና ክፉን የሚያሳውቀው ዛፍ።
16 ያህዌ እግዚአብሔር ለሰውየው አንድ ትእዛዝ ሰጠው። «በአትክልት ስፍራው ካለው ከማንኛውም ዛፍ ብላ። ከፈለግከው ዛፍ ሁሉ።»
18 ያህዌ እግዚአብሔር፣ «ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም። በትክክል የሚስማማውን ረዳት አደርግለታለሁ» አለ።