Deuteronomy 31

7 ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት አቆመው። እንዲህም አለው፣ «ጠንክር! ጀግና ሁን! ያህዌ ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደማለላቸው ምድር እነዚህን ሕዝቦች ይዘህ ትገባለህ። የራሳቸው አድርገው እንዲወስዱዋት ትረዳቸዋለህ።»

9 ሙሴ ይህንን ሕግ ጻፈው። የያህዌን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸከሙት ከሌዊ ነገድ ለሆኑት ካህናት ሰጣቸው። ለእስራኤል የሀገር ሽማግሌዎች ሁሉ ሰጣቸው።

30 ሙሴ የዚህን መዝሙር ቃል ሁሉ ለእስራኤል ተናገረ። ከመጀመሪያው ቃል እስከ መጨረሻው።