Deuteronomy 1
1 ሙሴ ይህንን ቃል ለእስራኤል ሁሉ ተናገረ። ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው በረሃ፣ ሜዳ በሆነው ሙቅና ደረቅ ምድር ቆመው ነበር። የሰፈሩትም ከሱፍ ፊት ለፊት፣ በፋራን፣ በጦፌል፣ በላባ፣ በሐጼሮትና በዲዛሃብ መካከል ነበር።
19 ከዚያም ከኮሬብ ወጣን። በዚያ ትልቅና የሚያስፈራ በረሃ ውስጥ ተጓዝን፤ በገዛ ዓይናችሁ አይታችሁታል! አምላካችን ያህዌ እንደነገረንም ወደ አሞራውያን ኮረብቶች አቀናን። ቃዴስ በርኔም ደረስን።
22 ነገር ግን ሁላችሁም ወደ እኔ መጣችሁ። እናንተም፣ "በቅድሚያ ከፊታችን ሰዎችን እንላክ። ምድሪቱን ሄደው ይዩ። ከዚያም በየትኛው መንገድ እንደምንሄድና የትኞቹን ከተሞች እንደምናገኝ ተመልሰው ይንገሩን" አላችሁ።