Genesis 46
1 እስራኤል ያለውን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሳ። መንገዱንም ጀመረ። ቤርሳቤህ ላይ አረፈ። እዚያም እንስሳትን አርዶ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሰጠ።
5 ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሳ። ፈርዖን በላካቸው ሠረገላዎች ላይ ልጆቹ አስገቡት። ሕፃናቶቻቸውንና ሚስቶቻቸውንም አሳፈሩ።
28 ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲያገኝ ይሁዳን አስቀድሞ ላከው። ይሁዳ ወደ ጎሼን የሚወስደውን መንገድ ያሳያቸው ነበር። ከዚያም ቤተሰቡ ሁሉ ጎሼን ደረሰ።
29 ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጀ። አባቱን እስራኤልን በጎሼን ለመቀበል ሮጦ ወጣ! እንዳየውም ዮሴፍ በአባቱ አንገት ላይ ተጠመጠመ። ለረጅም ጊዜም አለቀሰ።
31 ዮሴፍ ለወንድሞቹ እና በአባቱ ቤት ላሉት ሁሉ፣ "ፈርዖንን ለማየት እሄዳለሁ። ከእኔ ጋር ለመሆን ከከነዓን እንደመጣችሁ እነግረዋለሁ" አላቸው።