Genesis 38

1 በዚያን ጊዜ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለየ። ዓዱላማዊ ከሆነው ሒራ ከተባለ ጓደኛው ጋር ሊኖር ሄደ።

6 ይሁዳ ለትልቁ ልጁ ለኤር ሚስት መረጠለት። ስሟ ትዕማር ነበር።

12 ዓመታት አለፉ። የይሁዳ ሚስት ሞተች። ማልቀሱን ካቆመ በኋላ፣ የበጎቹን ፀጉር ለመሸለት ወደ ተምና ወጣ። ጓደኛው ሒራም አብሮት ሄደ።

20 ይሁዳ ፍየሉን በጓደኛው በሒራ እጅ ላከው። ሒራ ዕቃዎቹን ከሴትዮዋ ሊመልስ ሄደ። ሊያገኛት ግን አልቻለም።