Genesis 18
1 ያህዌ በመምሬ አጠገብ ባሉት ትልልቅ ዛፎች ዘንድ ታየው። አብርሃም በድንኳኑ በር ላይ ተቀምጦ ነበር። ፀሐይ ከላይ ትፋጅ ነበር።
16 ሰዎቹ ተነሱ። ፊታቸውንም ወደ ሰዶም አዞሩ። አብርሃም ሊሸኛቸው አብሯቸው ሄደ።
22 ሰዎቹ ፊታቸውን አዙረው ወደ ሰዶም መሄድ ጀመሩ። አብርሃም ግን እዚያው ቆየ፣ ከያህዌ ፊት ለፊት ቆሞ ነበር።
26 ያህዌም እንዲህ አለ፦ "በሰዶም ውስጥ አምሳ ጥሩ ሰዎች ባገኝ፣ በእነርሱ ምክንያት ከተማዋን ሁሉ አተርፋለሁ።"