Genesis 15

1 በኋላ ያህዌ በሕልም ለአብራም ተናገረ። "አብራም አትፍራ። እኔ እዚህ ነኝ። እኔ ጋሻህ ነኝ። እጠብቅሃለሁ። እኔ ሽልማትህ ነኝ። ከሁሉም ነገር እበልጣለሁ!"

4 ያህዌም መለሰ። "አይሆንም! ያ ሰው ንብረትህን አይወስድም። ልጅህ ይወስዳል። ከገዛ አካልህ የሚወጣ ልጅ!"

9 ያህዌ እንዲህ አለ፣ "ላም፣ ፍየል፣ እና አውራ በግ አምጣልኝ። ሁሉም የሦስት ዓመት የሆኑ። እንዲሁም እርግብና የርግብ ጫጩት አምጣ።"

11 ትላልቅ ወፎች ከሰማይ ወረዱ! ሥጋውን ፈለጉ። አብራም እጆቹን አወዛወዘ። አባረራቸው።

12 ፀሐይ ጠለቀች። አብራምን ከባድ እንቅልፍ ጣለው። መንቃት አልቻለም። አስፈሪና ድቅድቅ ጨለማ ከበበው።